ለዚህ ብሎግ የመጀመሪያና
የሙከራ ጽሑፍ ነው፡፡መልካም ንባብ
እንደ ክርስትያን በምድር ላይ ስንኖር እጅግ ክብር ከምንሰጠው ነገር ቢኖር ሃይማኖት ነው፡፡እኛ ኦርቶዶክሳውያን ለሃይማኖታችን ልዩ ክብርና ፍቅር አለን፡፡ነገር ግን አንዳንዶቸ የምንሰጠውን ክብር በመቃወም ሃይማኖትን ራሱን ሲያጣጥሉና ሲያክፋፉ ይታያሉ ፡፡በዚህ ረገድ በተለይ አንዳንድ የፕሮቴስታንት ክፍሎች የሚሰጡት አስተያየት በቀጥታ ኢ-መጽሐፋዊ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡
ፕሮቴስታንቶች ’’ሃይማኖት አያድንም’’ ፣ ’’እኛ ሃይማኖትን አንሰብክም ’’ ፣ ’’ያለ ምንም ሃይማኖት እንዲሁ ጌታን በግሌ አምናለሁ …. ወዘተ ’’ የሚለው አነጋገራቸው የብዙ የዋህን ልብ አድክሞ ብዙዎችን ’’ሃይማኖትን’’ እንደ ተራ ነገር እንደሚለከቱት ከማድረጉ ባሻገር ወደ ሃይማኖት አልባነት መርቷአቸዋል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው የተቃዋሚዎች ሐሳብ ከሐዋርያት ትምህርት እና እምነት ፈጽሞ የራቀ ነው ፡፡ሐዋርያት ለሃይማኖት ከፍተኛ ክብር ይሰጡ እንደነበር እስኪ ከመጽሐፈ ቅዱስ ጠቅሰን በከፊል እንመልከት፡-
መቼም ሰው ሊሞት ሲል የሚናገረው ቃል እጅግ ወሳኝ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደልም፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ ከተናገራቸው እጅግ ወሳኝ ቃላት ውስጥ አንዱ ’’ሃይማኖትን’’ የተመለከተ ነበር ፡፡’’ሃይማኖቴን ጠብቂያለሁ’’ የሚል 2ጢሞ.4፡7፡፡በተጨማሪም ጥቅሱ የሚያመለክተን ነገር ቢኖር ሃይማኖት ሊጠበቅ የሚገባው ክቡር ነገር መሆኑንና ለመጪው ሰማያዊ ሕይወታችን ሃይማኖት ወሳኝ ነገር መሆኑን ነው ፡፡
ሐዋርያው ይሁዳም ስለ ሃይማኖት የመከረው ትርታ እና ጥቅም እንደሌለው ነገር አድርጐ ሳይሆን በታላቅ አጽንኦት ነው ’’እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ ……..ጠብቁ ’’ ይሁዳ ቁ 20፡፡በተጨማሪም ’’ገንዘብ መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነውና አንዳንዶች የህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ስቃይ ራሳቸውን ወጉ ’’ ተብሏል 1ጢሞ 6፡10
ስለ ዘመናችንም ሲናገር ’’በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንት ትምህርት እያዳመጡ ሃይማኖት ይክዳሉ’’ በማለት ተናግሯል 1ጢሞ 4፡2፡፡ ቤተክርስትያን ግን ልጆቿ በሃይማኖት ነቅዕ እንዳይኖርባቸው በብርቱ ትወቅሳለች፡፡’’በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው’’ እንዲል ቲቶ 1፡14 ፡፡
ሃይማኖት የሚያክፋፉ ክፍሎች በእነርሱ አመለካከት ለጌታ እየቀኑ እየመሰላቸው ይሆናል፡፡ነገር ግን ጌታችን ’’የሃይማኖት ሐዋርያና ሊቀ ካህናት’’ተብሎ መጠራቱን ሊያስታውሱ ይገባል ፡፡ዕብ 12፡12
የሚገርመው ሌላኛው አባባለቸው ’’እኛ ክርስቶስን እንጂ ሃይማኖትን አንሰብክም ’’የሚለው ነው፡፡ነገር ግን ክርስቶስን መስበክ ማለት ሃይማኖት መስበክ ማለት መሆኑን የዘነጉት ይመስላል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስን በአሳዳጅነት ሕይወት በፊት ያውቁት የነበሩ ሰዎች ተመልሶ ክርስቶስን(ሃይማኖትን) ሲሰብክ ተመልክተው የተናገሩትን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ’’ቀድሞ እኛን ያስድ የነበረ፣እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረው ሃይማኖት አሁን ይሰብካል፡፡’’ ገላ 1፡23 ብለዋል፡፡
እኛ ግን ሃይማኖት በማክፋፉት ሳይሆን በክብር እንይዛለን፡፡ሃይማኖታችንም በክርስቶስ መሆኑን እናውቃለን ፡፡ሃይማኖትንም በዘፈቀደ የምናምነው ሳይሆን አንድ ግዜ ለሐዋርያት እንደተሰጠው እናምናለን፡፡የመጀመርያው በሐዋርያት የነበረ እምነት ወይም ሃይማኖት ለእኛ እነደ ደረሰ አውቀን በሃይማኖት እንኖራለን፡፡
ሃይማኖት ተራ ነገር ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ጳውሎስ’’አንዲት ሃይማኖትእንደማይል ’’ እናምናለን፡፡ሃይማኖት ተራ ነገር ቢሆን ኖሮ’’ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ ’’ ተብሎ የተጋድሎ ጥሪ ሊቀርብ እንደማይችል እናምናለን ይሁዳ ቁ.3፡፡ሃይማኖት ወሰኝ ነገር ባይሆን ኖሮ ’’ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ’’ የሚል ማስጠንቀቂያ ባልተነገረ ነበር፡፡ዕብ 4፡14 ሐዋርያት ሃይማኖትን በተመለከተ እንዲህ አስተምረዋል፡፡ተቃዋሚዎች ግን…..
ይቆየን !!!
ሳሙኤል ፍቃዱ
ነገረ ሃይማኖት (ዘኦርቶዶክስ) ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ ፡፡
ሃይማኖት ተራ ነገር ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ጳውሎስ’’አንዲት ሃይማኖትእንደማይል ’’ እናምናለን፡፡ሃይማኖት ተራ ነገር ቢሆን ኖሮ’’ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ ’’ ተብሎ የተጋድሎ ጥሪ ሊቀርብ እንደማይችል እናምናለን ይሁዳ ቁ.3፡፡ሃይማኖት ወሰኝ ነገር ባይሆን ኖሮ ’’ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ’’ የሚል ማስጠንቀቂያ ባልተነገረ ነበር፡፡ዕብ 4፡14 ሐዋርያት ሃይማኖትን በተመለከተ እንዲህ አስተምረዋል፡፡ተቃዋሚዎች ግን…..
ReplyDeleteE/R yaberetahe des yemil tsehufe newo