Saturday, July 7, 2012

በቂና አስፈላጊ


                                    በቂና አስፈላጊ

በስነ አምክንዮ "በቂ" እና "አስፈላጊ" የሚሉት ቃላቶች በጣም የጠራ ትጓሜና አጠቃቀም አላቸው።

                                                         
                                    አስፈላጊ ሁኔታ

መጀመሪያ ምሳሌዎችን እንይ፡
ለማየት አይን አስፈላጊ ነው -- ሲተረጎም፣ ለማየት የአይን መኖር መሟላት አለበት። በሌላ አነጋገር አይን ከሌለ ማየት አይቻልም።
አባት ለመሆን ወንደ መሆኑ አስፈላጊ ነው። -- ሲተረጎም የመጀመሪያው ድንጋጌ (አባትነት) እውነት እንዲሆን የጾታው ወንድ መሆን መሟላት አለበት።
P የተባለ አረፍተ ነገር (ድንጋጌ) Q ለተባለ ድንጋጌ እውነት መሆን አስፈላጊ ነው ከተባለ በግልባጭ ሲተረጎም "P እውነት እንዲሆን የግዴታ Q እውነት መሆን አለበት ," ወይም " P ውሸት ከሆነ Q ም ውሸት ነው" እንደማለት ይቆጠራል። ለምሳሌ ማየት በQ ቢወከልና አይን በP ቢወከል፣ P ለመሆን Q አስፈላጊ ነው። Q ከሆነ (ከታየ)፣ P እውነት ነው ማለት ነው (አይን አለ)።
ይህ ጉዳይ በሂሳብ ጥናት በቀላሉ እንደዚህ ይጻፋል፡ (Q => P), ትርጉሙም P የ"Q " መዘዝ ነው ማለት ነው። ወይም በሌላ አነጋገር Q እውን ሲሆን Pን ያመላክታል ማለት ነው። ምሳሌ፡ እይታ => አይን መኖር ፤ እይታ መፈጠሩ አይን መኖርን ያመላክታል። ወይም ደግሞ አይን መኖር የእይታ መዘዝ ነው።
                                     በቂ ሁኔታ
ምሳሌዎች፡
እንስሳ ለመሆን ድመት መሆን በቂ ነው -- ሲተረጎም፡ አንድ ነገር ድመት መሆኑን ካረጋገጥን እንስሳ መሆኑ አያጠራጥርም
አሜሪካዊ ለመሆን አሜሪካ መወለድ በቂ ነው -- ሲተረጎም፡ አንድ ሰው አሜሪካ ከተወለደ አሜሪካዊ መሆኑ አያጠራጥርም
P የተባለ አረፍተ ነገር Q የተባለ አረፍተ ነገር እውነት እንዲሆን በቂ ፣ ነው ካልን P እውነት መሆኑ ብቻ Qን እውነት ያደርገዋል። በሌላ ጎን P ውሸት ቢሆን Q ውሸት ነው ለማለት በቂ ማስረጃ የለንም። በሌላ አነገጋገር " P ከሆነ Q" ወይም ደግሞ "P => Q," በሚል ሲያጥር፣ " የP መሆን Qን ያመላክታል" ማለት ነው። ከዚህ አንጻር Q የP መዘዝ ነው ማለት ነው።
                                       ሂሳባዊ ግንኙነት
ሂሳብ ጥናት "በቂ" እና "አስፈላጊ" የተገላቢጦሽ ግንኙነት አላቸው። ለQ፣ P አስፈላጊ ከሆነ፣ ለP፣ Q በቂ ነው ማለት ነው። ምሳሌ፡ ድመት ለመሆን እንስሳ መሆን አስፈላጊ ሲሆን፣ በአንጻሩ እንስሳ ለመሆን ድመት መሆን በቂ ነው።
                                        በቂና አስፈላጊ
P ፣ ለ Q በቂና አስፈላጊ ነው ካልን ትርጉሙ "P ከሆነ Q እንዲሁም Q ከሆነ P" ወይም ባጭሩ "P ከሆነና ከሆነ ብቻ Q" እንደማለት ነው። በሂሳብ ሲጻፍ P Q ማለት ነው። P ና Q በዚህ ወቅት ምንም ልዩነት የላቸውም፣ አንድ ናቸው ማለት ይቻላል።
ምሳሌዎች:
ፀሐይ ለመባል ለምድር በጣም ቅርብ የሆነች ኮኮብ መሆን በቂና አስፈላጊ ነው --- ትርጉሙ ለምድር ከጸሃይ የሚቀርብ ኮኮብ ስሌለ፣
ምንጭ ፡-ውክፔዲያ

Tuesday, May 8, 2012

ቆይ ቆይ አሁን አንተ ምን እየሰራህ ነው ?


አንድ ድርጅት ልመናን ለማጥፋት በሚል የሆነ እንቅስቃሴ ይጀምራል፡፡ከዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዱ አካል የሆነው ታዲያ ባለሀብቶች ጋር በመሄድ ለስራው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማሰባሰብ ነበር ፡፡እናም ከተማው ውስጥ ካሉ አንድ ባለሀብት ጋር ይሄዱና የመጡበትን ነገር ሲነግሯቸው ልመናን ለማጥፋት በተቀቋቋምን ድርጅት ውስጥ ያለን ሰራተኞች ነን ….. ብለው ሳይጨርሱ በመሃል ባለሀብቱ ’’ጥሩ’’ ’’ጥሩ’’ ልመናማ መጥፋት አለበት አሏቸው፡፡ሰራተኞቹም ሲቀጥሉ እናም እርሶ ደግሞ እንደሚታወቀው ባለሃብት ኖት እናም አቅሞት የቻለውን ቢለግሱን ……..? ምን አልክ ? አቅሞት ቻለውን ቢለግሱን ? ለምን ? ያው ልመናን ለማጥፋት ?…… ቆይ ቆይ አሁን አንተ ምን እየሰራህ ነው ? ብለውት እርፍ፡፡እኔ የባለሀብቱን አካሄድ ስረዳው ልመናውን ለምን ከዚሁ አናቆመውም አይነት ነገር ነው የተረዳሁት(ልመናን ከምንጩ ማድረቅ)፡፡እናንተስ ??

Friday, May 4, 2012

የተስፋዬ ለማ እይታዎች: እግዚአብሔር ከእኔ ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ለመሆን ፈቃደኛ ከሆነ ታድያ እንደ ኃ...

የተስፋዬ ለማ እይታዎች: እግዚአብሔር ከእኔ ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ለመሆን ፈቃደኛ ከሆነ ታድያ እንደ ኃ...:     ተገቢውን ተግሳጽ ተደራረጉ ነገር ግን አትወነጃጀሉ፣ተመካከሩ ነገር ግን ቧልት አይሁን፡፡ተደጋገፉ ግን አታሲሩ፡፡ስትነቃቀፉ ግን ስለማን እና ስለምን እንደሆነ አስተውሉ፡፡በቤተክርስትያናዊ መንፈስ እንደምትከባበሩ...

የተስፋዬ ለማ እይታዎች: እግዚአብሔር ከእኔ ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ለመሆን ፈቃደኛ ከሆነ ታድያ እንደ ኃ...

የተስፋዬ ለማ እይታዎች: እግዚአብሔር ከእኔ ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ለመሆን ፈቃደኛ ከሆነ ታድያ እንደ ኃ...:     ተገቢውን ተግሳጽ ተደራረጉ ነገር ግን አትወነጃጀሉ፣ተመካከሩ ነገር ግን ቧልት አይሁን፡፡ተደጋገፉ ግን አታሲሩ፡፡ስትነቃቀፉ ግን ስለማን እና ስለምን እንደሆነ አስተውሉ፡፡በቤተክርስትያናዊ መንፈስ እንደምትከባበሩ...

እግዚአብሔር ከእኔ ከኃጢአተኛው ጋር አንድ ለመሆን ፈቃደኛ ከሆነ ታድያ እንደ ኃጢአተኛ ከሆነ ወንድሜ ጋር አንድ እንዳልሆን የእኔ ትእቢት ከምን የመጣ ነው ? እግዚአብሔር ካልፈቀደ በቀር ተሰብስቦ በማኅበር መሥራት ቀርቶ ሁለት ሆኖ በአንድ ቤት መኖር ይከብዳል፡፡ አትሮኖስ መጽሔት 2003


    ተገቢውን ተግሳጽ ተደራረጉ ነገር ግን አትወነጃጀሉ፣ተመካከሩ ነገር ግን ቧልት አይሁን፡፡ተደጋገፉ ግን አታሲሩ፡፡ስትነቃቀፉ ግን ስለማን እና ስለምን እንደሆነ አስተውሉ፡፡በቤተክርስትያናዊ መንፈስ እንደምትከባበሩ እንደምታከብሩን ንገሩን ፡፡ደግሞም በተግባር  አሳዩን ፡፡የቡድንተኝነት ስሜትን አስወግዱ፡፡መካሪውንም ተማካሪውንም ፣ ነቃፊውንም ተነቃፊውንም፣ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቅድስት ቤተክስትያን ትፈልጋችኋለችና፡፡
   

     እናስተውል ስለ እግዚአብሔር እና ለእግዚአብሔር ብሎ ከሚያገለግል ከሥጋ ፍላጎት የተነሳ መንፈሳዊ ዝለት  ገጥሞት በአግልግሎቱ ላይ እንከን ሊገጥመው ይችላል፡፡ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ሰዎችን ስነነቅፋቸው፣ስነገስጻቸው፣ስናርማቸው ፍጹም ክርስትያናዊ እና ቤትክርስትያናዊ ስርዓትን በተከተለ መንገድ ሊሆን  ይገባናል ፡፡እኔ ወንድሜን ዘረኛ ብዬ ልነቅፍ ተነስቼ  ይሆናል፡፡ግን እኔ እራሴ ምን  ያህል ከዘረኝነት አስተሳሰብ የጸዳው ነኝ?፤ ወንድሜን ምዳይ ምጽዋት ገልባጭ ስለው እኔ እራሴ እድሉን ባገኝና ቢመቸኝ ምዳይ ምጽዋቱን ላለመንካት ምን ያህል የታመንኩ ነኝ ? ልንል ይገባል ፡፡ በእርግጥ እነዚህን እና መሰል ችግሮች በገሃድ እየታዩ ሊሆን ይችላል ግን ለማስተካከል፣ በድጋሚ ችግሩ እንዳይከሰት የምንጠቀምባቸው መንገዶች ግን ፍጹም ክርስትያናዊና ቤተክርስትያናዊ አካሄድ ሊሆን ግን ይገባል፡፡ እንዲህ አይነት ስራ የሚሰሩትን ከሰማይ መብረቅ ወርዶ እንዲቀስፋቸው የምንፈለግም ሰዎችም አለን እንዲህ አይነት መንፈስ ግን ፍጹም ክርስትያናዊ አይደለም፡፡


      አዎ ! ጠላቶቻችን ያልናቸው ሰዎች እኛንም ቤተክርስትያንንም በድለው ይሆናል፡፡ግን እኛ እራሳችንንና ቤተክርስትያንን ከበደልነው አይብስም፡፡ወይም እኛ እራሳችን እና ቤተክርስትያንን ከበደልነው በላይ አልበደሉንም፡፡ስለዚህ እኛ ላጠፋነው የሚገባውን ቀኖና እንጠይቅበት፡፡የሌሎችን ግን ለበለቤቱ እንተውለት፡፡ፍርድ የኔነው ብሏልና፡፡ክርስትናው አባቶችም ያስተማሩን ስርዓትም እንደዚህ ነውና፡፡እኛ እግዚአብሔርን የበደልነውን ስርየት ሳይሰጠን የሌሎችን ቅጣትና መቀጣትን አያሰየንም፡፡ የሌሎችንም (የወንድሞቻችን) መቀጣት መናፈቅ የለብንም፡፡ደግሞ እግዚአብሔር እኛን ታግስሶ የሌሎችን መቀጣት ብናይም እኛ ለሰራነው ኃጢአት የንስሃ እድሜ እየሰጠን እንጂ የሰራነው ኃጢአት ትክክል ነው እያለን እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባል፡፡


       በዚህ ላይ ደግሞ ቃላቶችን ሳንመርጥ የምንሰጣቸው  አስተያቶችና እና የምንጽፋቸው ጽሑፎች ላይ ጥንቃቄ እናድርግ፡፡አሁን እንደዚህ ስርዓት በጎደለው እና ፍጹም የቤተክርስትያን ቃል በማይመስል አኳኋን የምንሰጣቸው አስተያየቶችና ትችቶች መናፍቃንና አህዛቦች ቢሆኑ ነሮስ ? ስለዚህ እነሱ ያላደረጉትን እኛ የአንዲት እናት ቅድስት ቤተክርስትያን ልጆች ታዲያ ስለምን እንደምንጽፍ ማስተዋል ተሳነን ? ስለዚህ የተመረጡ ቃላቶችን እና (ቤተክስትያነዊ ለዛ) ያለቸውን፣መፍትሄ ጠቋሚ የሆኑ አስተያየቶችን በመስጠትና አንድ በመሆን ለሌሎች ማለት የእኛን ልዩነት ለሚፈልጉ አካሎች እንደቀደመው ዘመን ስጋት ልንሆንባቸው ይገባል፡፡አዎ ! ትልቅ እና አንድ የመሆን ስጋት፤ በጎ የመሆን ስጋት፡፡
      

      የመመካከራችሁና የመተራረማችሁ ነገር በፍቅርና ስለፍቅር ይሁን፡፡ደግሞ እናንተ ብቻ አይደላችሁም መካሪ እኛም ልንመክራቸሁ እድሉን ስጡን፡፡ደግሞም ስንመክራችሁ እሺ በሉ፡፡ምን አጠፋን ? በሉ፡፡በአገልግሎታችን ላይ ምን አገኛችሁብን ? ምን አያችሁብን ? ልትሉን ይገባል፡፡ምክንያቱም አንዳንዴ እንደ ጽድቅ የያዛችሁት መንጋውን የሚያስጨንቅ ፣ እርስ በእርስ መተማመንን የሚያጠፉ ነገሮች አጀናዳዎቻችሁ ውስጥ ስለሚኖራችሁ፡፡ስለዚህ የሁላችንም ቤት በሆነችው ቅድስት ቤተክርስትያን ውስጥ ተሰብስበን እና ተጠራርተን የምንመካከርባቸው እና የምንማማርባቸው ትልልቅ ጉባኤዎች ሊዘረጉ ግድ ይላል፡፡ወይም ያስፈለገናል፡፡


      ስለዚህ ማኅበርተኞችም ሆናችሁ ቡድንተኞች አገልግሎታችሁ ሁሉ ስለ ህንጻ ቤተ ክርስትያን ግንባታ ብቻ ውስጡም ስላው አሰተዳደራዊ ሁኔታ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ስለትውልድም ግንባታ እና ስለወደፊቱ መጻኢ ጊዜ እንዲሁም የአባቶችን አደራ ስለሚያስጠብቅ ትውልድ ስለማፍራት መሆን አለበት፡፡ምክንያቱም ከእናንተው በመጣ አለመግባባትና አለመደማመጥ በኛ ውስጥ ከፍርሃትና ከትካዜ የተነሳ እየተጨነቅን ስለሆነ መግባባት እንደምትችሉ፣የተፈጠሩት ችግች በመነጋገርና በመከባባር መንፈስ ተሆኖ ያሉ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚችል፣እንደምትዋደዱ፣አንድ እንደሆናችሁ ትልቅ ጉባኤ ዘርጉና አሳውቁን ፡፡


እግዚአብሔር ሀገራችንና ሃይማኖታችንን ይብቅልን፡፡ አሜን !!
        

            ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይህ ጽሑፍ ከተጻፈ ቢቆይም እግዚአብሔር ፈቅዶ ይኸው አሁን አወጣሁት፡፡


Wednesday, May 2, 2012

ሃይማኖት ማክፋፋት ’’ሃይማኖት አያድንም’’ ???





ለዚህ ብሎግ የመጀመሪያና የሙከራ ጽሑፍ ነው፡፡መልካም ንባብ


እንደ ክርስትያን በምድር ላይ ስንኖር እጅግ ክብር ከምንሰጠው ነገር ቢኖር ሃይማኖት ነው፡፡እኛ ኦርቶዶክሳውያን  ለሃይማኖታችን ልዩ ክብርና ፍቅር አለን፡፡ነገር ግን አንዳንዶቸ  የምንሰጠውን ክብር በመቃወም ሃይማኖትን ራሱን ሲያጣጥሉና ሲያክፋፉ ይታያሉ ፡፡በዚህ ረገድ በተለይ አንዳንድ የፕሮቴስታንት ክፍሎች የሚሰጡት አስተያየት በቀጥታ ኢ-መጽሐፋዊ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡
    ፕሮቴስታንቶች ’’ሃይማኖት አያድንም’’ ’’እኛ ሃይማኖትን አንሰብክም ’’ ’’ያለ ምንም ሃይማኖት እንዲሁ ጌታን በግሌ አምናለሁ …. ወዘተ ’’ የሚለው አነጋገራቸው የብዙ የዋህን ልብ አድክሞ ብዙዎችን ’’ሃይማኖትን’’ እንደ ተራ ነገር እንደሚለከቱት ከማድረጉ ባሻገር ወደ ሃይማኖት አልባነት መርቷአቸዋል፡፡
    ከላይ የተጠቀሰው የተቃዋሚዎች ሐሳብ ከሐዋርያት ትምህርት እና እምነት ፈጽሞ የራቀ ነው ፡፡ሐዋርያት ለሃይማኖት ከፍተኛ ክብር ይሰጡ እንደነበር እስኪ ከመጽሐፈ ቅዱስ ጠቅሰን በከፊል እንመልከት፡-
    መቼም ሰው ሊሞት ሲል የሚናገረው ቃል እጅግ ወሳኝ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደልም፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ ከተናገራቸው እጅግ ወሳኝ ቃላት ውስጥ አንዱ ’’ሃይማኖትን’’   የተመለከተ ነበር ፡፡’’ሃይማኖቴን ጠብቂያለሁ’’ የሚል 2ጢሞ.4፡7፡፡በተጨማሪም ጥቅሱ የሚያመለክተን ነገር ቢኖር ሃይማኖት ሊጠበቅ የሚገባው ክቡር ነገር መሆኑንና ለመጪው ሰማያዊ ሕይወታችን ሃይማኖት ወሳኝ ነገር መሆኑን ነው ፡፡
    ሐዋርያው ይሁዳም ስለ ሃይማኖት የመከረው ትርታ እና ጥቅም እንደሌለው ነገር አድርጐ ሳይሆን በታላቅ አጽንኦት ነው ’’እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ ……..ጠብቁ ’’ ይሁዳ ቁ 20፡፡በተጨማሪም ’’ገንዘብ መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነውና አንዳንዶች የህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ስቃይ ራሳቸውን ወጉ ’’ ተብሏል 1ጢሞ 6፡10
    ስለ ዘመናችንም ሲናገር ’’በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንት ትምህርት እያዳመጡ ሃይማኖት ይክዳሉ’’ በማለት ተናግሯል 1ጢሞ 4፡2፡፡ ቤተክርስትያን ግን ልጆቿ በሃይማኖት ነቅዕ እንዳይኖርባቸው በብርቱ ትወቅሳለች፡፡’’በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው’’ እንዲል ቲቶ 1፡14 ፡፡
    ሃይማኖት የሚያክፋፉ ክፍሎች በእነርሱ አመለካከት ለጌታ እየቀኑ እየመሰላቸው ይሆናል፡፡ነገር ግን ጌታችን ’’የሃይማኖት ሐዋርያና ሊቀ ካህናት’’ተብሎ መጠራቱን ሊያስታውሱ ይገባል ፡፡ዕብ 12፡12
     የሚገርመው ሌላኛው አባባለቸው ’’እኛ ክርስቶስን እንጂ ሃይማኖትን አንሰብክም ’’የሚለው ነው፡፡ነገር ግን ክርስቶስን መስበክ ማለት ሃይማኖት መስበክ ማለት መሆኑን የዘነጉት ይመስላል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስን በአሳዳጅነት ሕይወት በፊት ያውቁት የነበሩ ሰዎች ተመልሶ ክርስቶስን(ሃይማኖትን) ሲሰብክ ተመልክተው የተናገሩትን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ’’ቀድሞ እኛን ያስድ የነበረ፣እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረው ሃይማኖት አሁን ይሰብካል፡፡’’ ገላ 1፡23 ብለዋል፡፡
እኛ ግን ሃይማኖት በማክፋፉት ሳይሆን በክብር እንይዛለን፡፡ሃይማኖታችንም በክርስቶስ መሆኑን እናውቃለን ፡፡ሃይማኖትንም በዘፈቀደ የምናምነው ሳይሆን አንድ ግዜ ለሐዋርያት እንደተሰጠው እናምናለን፡፡የመጀመርያው በሐዋርያት የነበረ እምነት ወይም ሃይማኖት ለእኛ እነደ ደረሰ አውቀን በሃይማኖት እንኖራለን፡፡
     ሃይማኖት ተራ  ነገር ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ጳውሎስ’’አንዲት ሃይማኖትእንደማይል ’’  እናምናለን፡፡ሃይማኖት ተራ ነገር ቢሆን ኖሮ’’ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ ’’ ተብሎ የተጋድሎ ጥሪ ሊቀርብ እንደማይችል እናምናለን ይሁዳ ቁ.3፡፡ሃይማኖት ወሰኝ ነገር ባይሆን ኖሮ ’’ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ’’ የሚል ማስጠንቀቂያ ባልተነገረ ነበር፡፡ዕብ 4፡14 ሐዋርያት ሃይማኖትን በተመለከተ እንዲህ አስተምረዋል፡፡ተቃዋሚዎች ግን…..
                       ይቆየን  !!!
 ሳሙኤል ፍቃዱ

ነገረ ሃይማኖት (ዘኦርቶዶክስ) ከሚለው መጽሐፍ  የተወሰደ ፡፡