ተገቢውን ተግሳጽ ተደራረጉ ነገር ግን አትወነጃጀሉ፣ተመካከሩ ነገር ግን ቧልት አይሁን፡፡ተደጋገፉ
ግን አታሲሩ፡፡ስትነቃቀፉ ግን ስለማን እና ስለምን እንደሆነ አስተውሉ፡፡በቤተክርስትያናዊ መንፈስ እንደምትከባበሩ እንደምታከብሩን
ንገሩን ፡፡ደግሞም በተግባር አሳዩን ፡፡የቡድንተኝነት ስሜትን አስወግዱ፡፡መካሪውንም
ተማካሪውንም ፣ ነቃፊውንም ተነቃፊውንም፣ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቅድስት ቤተክስትያን ትፈልጋችኋለችና፡፡
እናስተውል ስለ እግዚአብሔር እና ለእግዚአብሔር ብሎ ከሚያገለግል ከሥጋ ፍላጎት የተነሳ መንፈሳዊ ዝለት ገጥሞት በአግልግሎቱ ላይ እንከን ሊገጥመው ይችላል፡፡ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ሰዎችን ስነነቅፋቸው፣ስነገስጻቸው፣ስናርማቸው ፍጹም ክርስትያናዊ እና ቤትክርስትያናዊ ስርዓትን በተከተለ መንገድ ሊሆን ይገባናል ፡፡እኔ ወንድሜን ዘረኛ ብዬ ልነቅፍ ተነስቼ ይሆናል፡፡ግን እኔ እራሴ ምን ያህል ከዘረኝነት አስተሳሰብ የጸዳው ነኝ?፤ ወንድሜን ምዳይ ምጽዋት ገልባጭ ስለው እኔ እራሴ እድሉን ባገኝና ቢመቸኝ ምዳይ ምጽዋቱን ላለመንካት ምን ያህል የታመንኩ ነኝ ? ልንል ይገባል ፡፡ በእርግጥ እነዚህን እና መሰል ችግሮች በገሃድ እየታዩ ሊሆን ይችላል ግን ለማስተካከል፣ በድጋሚ ችግሩ እንዳይከሰት የምንጠቀምባቸው መንገዶች ግን ፍጹም ክርስትያናዊና ቤተክርስትያናዊ አካሄድ ሊሆን ግን ይገባል፡፡ እንዲህ አይነት ስራ የሚሰሩትን ከሰማይ መብረቅ ወርዶ እንዲቀስፋቸው የምንፈለግም ሰዎችም አለን እንዲህ አይነት መንፈስ ግን ፍጹም ክርስትያናዊ አይደለም፡፡
አዎ ! ጠላቶቻችን ያልናቸው ሰዎች እኛንም ቤተክርስትያንንም በድለው ይሆናል፡፡ግን እኛ እራሳችንንና ቤተክርስትያንን ከበደልነው አይብስም፡፡ወይም እኛ እራሳችን እና ቤተክርስትያንን ከበደልነው በላይ አልበደሉንም፡፡ስለዚህ እኛ ላጠፋነው የሚገባውን ቀኖና እንጠይቅበት፡፡የሌሎችን ግን ለበለቤቱ እንተውለት፡፡ፍርድ የኔነው ብሏልና፡፡ክርስትናው አባቶችም ያስተማሩን ስርዓትም እንደዚህ ነውና፡፡እኛ እግዚአብሔርን የበደልነውን ስርየት ሳይሰጠን የሌሎችን ቅጣትና መቀጣትን አያሰየንም፡፡ የሌሎችንም (የወንድሞቻችን) መቀጣት መናፈቅ የለብንም፡፡ደግሞ እግዚአብሔር እኛን ታግስሶ የሌሎችን መቀጣት ብናይም እኛ ለሰራነው ኃጢአት የንስሃ እድሜ እየሰጠን እንጂ የሰራነው ኃጢአት ትክክል ነው እያለን እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባል፡፡
በዚህ ላይ ደግሞ ቃላቶችን ሳንመርጥ የምንሰጣቸው አስተያቶችና እና የምንጽፋቸው ጽሑፎች ላይ ጥንቃቄ እናድርግ፡፡አሁን እንደዚህ ስርዓት በጎደለው እና ፍጹም የቤተክርስትያን ቃል በማይመስል አኳኋን የምንሰጣቸው አስተያየቶችና ትችቶች መናፍቃንና አህዛቦች ቢሆኑ ነሮስ ? ስለዚህ እነሱ ያላደረጉትን እኛ የአንዲት እናት ቅድስት ቤተክርስትያን ልጆች ታዲያ ስለምን እንደምንጽፍ ማስተዋል ተሳነን ? ስለዚህ የተመረጡ ቃላቶችን እና (ቤተክስትያነዊ ለዛ) ያለቸውን፣መፍትሄ ጠቋሚ የሆኑ አስተያየቶችን በመስጠትና አንድ በመሆን ለሌሎች ማለት የእኛን ልዩነት ለሚፈልጉ አካሎች እንደቀደመው ዘመን ስጋት ልንሆንባቸው ይገባል፡፡አዎ ! ትልቅ እና አንድ የመሆን ስጋት፤ በጎ የመሆን ስጋት፡፡
የመመካከራችሁና የመተራረማችሁ ነገር በፍቅርና ስለፍቅር ይሁን፡፡ደግሞ እናንተ ብቻ አይደላችሁም መካሪ እኛም ልንመክራቸሁ እድሉን ስጡን፡፡ደግሞም ስንመክራችሁ እሺ በሉ፡፡ምን አጠፋን ? በሉ፡፡በአገልግሎታችን ላይ ምን አገኛችሁብን ? ምን አያችሁብን ? ልትሉን ይገባል፡፡ምክንያቱም አንዳንዴ እንደ ጽድቅ የያዛችሁት መንጋውን የሚያስጨንቅ ፣ እርስ በእርስ መተማመንን የሚያጠፉ ነገሮች አጀናዳዎቻችሁ ውስጥ ስለሚኖራችሁ፡፡ስለዚህ የሁላችንም ቤት በሆነችው ቅድስት ቤተክርስትያን ውስጥ ተሰብስበን እና ተጠራርተን የምንመካከርባቸው እና የምንማማርባቸው ትልልቅ ጉባኤዎች ሊዘረጉ ግድ ይላል፡፡ወይም ያስፈለገናል፡፡
ስለዚህ ማኅበርተኞችም ሆናችሁ ቡድንተኞች አገልግሎታችሁ ሁሉ ስለ ህንጻ ቤተ ክርስትያን ግንባታ ብቻ ውስጡም ስላው አሰተዳደራዊ ሁኔታ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ስለትውልድም ግንባታ እና ስለወደፊቱ መጻኢ ጊዜ እንዲሁም የአባቶችን አደራ ስለሚያስጠብቅ ትውልድ ስለማፍራት መሆን አለበት፡፡ምክንያቱም ከእናንተው በመጣ አለመግባባትና አለመደማመጥ በኛ ውስጥ ከፍርሃትና ከትካዜ የተነሳ እየተጨነቅን ስለሆነ መግባባት እንደምትችሉ፣የተፈጠሩት ችግች በመነጋገርና በመከባባር መንፈስ ተሆኖ ያሉ ችግሮች ሊፈቱ እንደሚችል፣እንደምትዋደዱ፣አንድ እንደሆናችሁ ትልቅ ጉባኤ ዘርጉና አሳውቁን ፡፡
እግዚአብሔር ሀገራችንና ሃይማኖታችንን ይብቅልን፡፡ አሜን !!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይህ ጽሑፍ ከተጻፈ ቢቆይም እግዚአብሔር ፈቅዶ ይኸው አሁን አወጣሁት፡፡
No comments:
Post a Comment